የቀይ ባሕር እና የናይል ወንዝ ተጠቃሚነት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ኅልውና እና ስትራቴጂያዊ ነፃነት ወሳኝ ነው - የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየቀይ ባሕር እና የናይል ወንዝ ተጠቃሚነት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ኅልውና እና ስትራቴጂያዊ ነፃነት ወሳኝ ነው - የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት
የቀይ ባሕር እና የናይል ወንዝ ተጠቃሚነት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ኅልውና እና ስትራቴጂያዊ ነፃነት ወሳኝ ነው - የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.10.2025
ሰብስክራይብ

የቀይ ባሕር እና የናይል ወንዝ ተጠቃሚነት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ኅልውና እና ስትራቴጂያዊ ነፃነት ወሳኝ ነው - የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት

የአገሪቱ ብልጽግና ከቀይ ባሕር እና ከናይል ተፋሰስ ጋር በመሠረታዊነት የተቆራኘ መሆኑን ያብራራው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ ይህ ተጠቃሚነት "የማንነት፣ የእርቅ እና የታሪካዊ ቀጣይነት" ጉዳይ መሆኑን አጽናኦት ሰጥቷል፡፡

ይህ አቋም የተንፀባረቀው "የናይል-ቀይ ባሕር ትስስር" በሚል ርዕስ በአፋር ክልል ዋና ከተማ በሰመራ በተደረገው ስትራቴጂያዊ ጉባኤ ላይ መሆኑን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ፣ በቀይ ባሕር ጂኦፖለቲካ ላይ ለዘመናት የቆየውን ዝምታ ማብቃቱን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ወደ ባሕሩ መቅረብ "ኃይል እና ራዕይዋ እንደሚሰፋ" አመላክተዋል።

በመድረኩ የአገሪቱን ጥቅም ለማስጠበቅ የኢትዮጵያን የባሕር ኃይል ዘመናዊና ብቁ ኃይል እንዲሆን ለማደራጀት እየተደረገ ያለውን ጥረትም ተገልጿል።

ሁለቱን የውኃ ሥርዓቶች በኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ አጀንዳ ውስጥ ለማዋሃድ ያለመው ይህ ጉባኤ፣ በከፍተኛ የመንግሥትና የጦር መኮንኖች ተሳትፎ መካሄዱን ሚዲያው ገልጿል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0