የአፍሪካ ልማት ባንክን በኢትዮጵያ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ መዋዕለ ነዋይ ፈሰስ እንደሚያደርግ አስታወቀ
17:39 19.10.2025 (የተሻሻለ: 17:44 19.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ልማት ባንክን በኢትዮጵያ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ መዋዕለ ነዋይ ፈሰስ እንደሚያደርግ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ልማት ባንክን በኢትዮጵያ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ መዋዕለ ነዋይ ፈሰስ እንደሚያደርግ አስታወቀ
የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሲዲ ኦልድ ታህ፣ ባንኩ በበጀት ድጋፍ፣ በግብርና እና በመሠረተ ልማት እና በተለይም ለቀጣናዊ ውህደት ወሳኝ ለሆነው የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ድጋፍ ለማድረግ ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከዓለም ባንክና ከዓለም ከአይኤምኤፍ ዓመታዊ ጉባኤ ጎን ለጎን ከባንኩ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱም የገንዘብ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚያዊ እና የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለማሻሻል፣ በዐቢይ ዘርፎች ላይ ምርታማነትን ለማሳደግ እና የመንግሥታዊ ዘርፍን ውጤታማነት ለማጠናከር ተግባራዊ የሆኑ የሪፎርም ጥረቶችን ለፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል።
የልማት ባንኩ ዋና መሪ አመቻች እና ገንዘብ አቅራቢ በመሆን ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ስላሚገኝበት አዲሱ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት የተመለከቱ መረጃዎችም በውይይቱ ውስጥ ተካተዋል ሲል ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ የትስስር ገፁ ላይ አስነብቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ልማት ባንክን በኢትዮጵያ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ መዋዕለ ነዋይ ፈሰስ እንደሚያደርግ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/