ሉቭረ ያጋጠመው ስርቆት በፈረንሳይ ሙዚየሞች ያለውን የደህንነት ጉድለት አጋልጧል - የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አምኗል
ሉቭረ ያጋጠመው ስርቆት በፈረንሳይ ሙዚየሞች ያለውን የደህንነት ጉድለት አጋልጧል - የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አምኗል
ከሉቭረ ሙዚየም የተሰረቀው ጌጣጌጥ "ትክክለኛ ባሕላዊ ቅርስ" ነው ሲሉ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሎውረንት ኑኜዝ ተናግረዋል።
ስለ ስርቆቱ የተሰሙ ተጨማሪ ዝርዝሮች፡-
◻ ሌቦቹ ዛሬ ማለዳ የሉቭረን ሙዚየም ሰብረው በመግባት የንጉሠ ነገሥት ናፖሊዮን ቀዳማዊ ባለቤት የነበሩት የእቴጌ ጆሴፊን ስብስብ የሆኑ ዘጠኝ ጌጣጌጦችን እንደሰረቁ የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
◻ የንጉሠ ነገሥት ናፖሊዮን ሳልሳዊ ባለቤት የነበሩት የእቴጌ ዩጂኒ ደ ሞንቲጆ የተሰበረ አክሊል በሉቭረ ሙዚየም አቅራቢያ ተገኝቷል (በምስል ላይ የሚታየው) ሲሉ የፈረንሳይ ሚዲያ ገልጿል።
◻ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ "ሦስት ወይም አራት" ሌቦች ስርቆቱን ያከናወኑት በ"ሰባት ደቂቃዎች" ውስጥ ነው። ሙዚየሙ ውስጥ ከውጭ በመግባት "አፖሎ ጋለሪ" ወደሚባለው ቦታ ለመድረስ በጭነት መኪና ላይ የተገጠመ ግንባታ እቃ ማቀበያ ማሽን ተጠቅመዋል (ቪዲዮ 2)።
◻ የፓሪስ ዓቃቤ ሕግ ቢሮ በጉዳዩ ላይ በተደራጀ ስርቆት እና በወንጀል ሴራ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።
በፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ የተቀረጸው ቪዲዮ ከዝርፊያው በኋላ በፓሪስ ሉቭረ ሙዚየም አካባቢ ያለውን ሁኔታ ያሳያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
