ሐማስ አሜሪካን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሷል በማለት ያቀረበችበትን ክስ አስተባበለ
16:49 19.10.2025 (የተሻሻለ: 16:54 19.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሐማስ አሜሪካን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሷል በማለት ያቀረበችበትን ክስ አስተባበለ
ፍልስጤማዊው ንቅናቄ በመግለጫው የሚከተሉትን ነጥቦችንም አስታውቋል፡-
በመሬት ላይ ያለው እውነታ እንደሚያሳየው የወራሪው አካል ባለሥልጣናት "በጋዛ ሰርጥ የወንጀል ቡድኖችን አደራጅተዋል፣ አስታጥቀዋል እንዲሁም በገንዘብ ደግፈዋል"።
ሐማስ የአሜሪካን አስተዳደር "የወራሪውን አካል ትርክት ማስተጋባት እንዲያቆም እና በምትኩ የተኩስ አቁም ስምምነትን መጣስ ላይ እንዲያተኩር" አሳስቧል።
በንቅናቄው ላይ የሚሰነዘሩት የሐሰት ክሶች "ከእስራኤል ፕሮፓጋንዳ ጋር የሚጣጣሙ እና የወራሪው አካል ባለሥልጣናት ለሚፈጽሟቸው ተከታታይ ወንጀሎችና ጥቃቶች እንደ ሽፋን ሆነው ያገለግላሉ"።
በትናንትናው ዕለት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እንዳስታወቀው፤ አሜሪካ ስለ ሐማስ "በቅርቡ የሚፈፀም" የተኩስ አቁም ስምምነት ጥሰት ለጋዛ ሰላም ስምምነት ዋስትና ለሰጡ አገሮች አሳውቃ ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/