የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል የምክክር አጀንዳ ሊያሰባስብ መሆኑን አስታወቀ
16:14 19.10.2025 (የተሻሻለ: 16:24 19.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል የምክክር አጀንዳ ሊያሰባስብ መሆኑን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል የምክክር አጀንዳ ሊያሰባስብ መሆኑን አስታወቀ
ለተግባራዊነቱ የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ምላሽ እየተጠባበቀ ይገኛል ሲሉ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
አክለውም በክልሉ የ94 ወረዳዎች ተወካዮችን ለመምረጥ እና ለውይይቱ አስፈላጊ መደላድሎችን ለመፍጠር ጊዜያዊ አስተዳደር ቃል መግባቱን ፕሮፌሰር መስፍን ጠቁመዋል። በክልሉ የሚደረገው አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ መጠናቀቅ የኢትዮጵያን ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መጠራትን ሊያፋጥን እንደሚችልም አስረድተዋል።
ኮሚሽኑ አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ መስተዳድሮችን ጨምሮ በ11 ክልሎች የተለያዩ የኅብረተሰብ ተወካዮችን በማሳተፍ አጀንዳ አሰባስቧል፡፡ ከሀገር ውጭም በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት፣ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በማሳተፍ ውይይት ተካሂዶ ጠቃሚ ግብዓት ማሰባሰቡን አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X