የኢትዮጵያ የወርቅ ዋጋ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ100% አድጎ 25 ሺህ ብር መድረሱ ተዘገበ
15:18 19.10.2025 (የተሻሻለ: 15:24 19.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ የወርቅ ዋጋ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ100% አድጎ 25 ሺህ ብር መድረሱ ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የወርቅ ዋጋ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ100% አድጎ 25 ሺህ ብር መድረሱ ተዘገበ
ከአንድ ወር በፊት የአንድ ግራም ዋጋ ከ18 ሺህ 500 እስከ 19 ሺህ ብር አካባቢ ነበር፤ ይህ የወርቅ ዋጋ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ መጨመሩን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ጭማሪው የአገር ውስጥ የኢኮኖሚ ጫናዎችን እና ዓለም አቀፍ የገበያ ሁኔታዎችን የሚያንፀባርቅ ሲሆን የአገር ውስጥ የዋጋ ግሽበት ሰፋፊ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴዎችን ተከትሎ የመጣ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።
ዓለም አቀፍ የወርቅ ዋጋ እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2020 ከነበረበት 1,885 ዶላር በዚህ ወር ወደ 4,250 ዶላር በመጨመር በግምት 125% አድጓል።
እንደ ዘገባው ከሆነ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የወርቅ ዋጋ ባለፉት አምስት ዓመታት በግምት 800% ጭምሯል፡፡ ይህም ከዓለም አቀፉ የዶላር ጭማሪዎችን በእጅጉ ይበልጣል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X