በ2017 የበጀት ዓመት ከ68 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሠረታዊ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓት ተሰራጭቷል ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበ2017 የበጀት ዓመት ከ68 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሠረታዊ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓት ተሰራጭቷል ተባለ
በ2017 የበጀት ዓመት ከ68 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሠረታዊ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓት ተሰራጭቷል ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.10.2025
ሰብስክራይብ

በ2017 የበጀት ዓመት ከ68 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሠረታዊ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓት ተሰራጭቷል ተባለ

በስርጭቱ 22 ሺህ መንግሥታዊ የጤና ተቋማት ተጠቃሚ መሆናቸው በ7ኛው ሀገር አቀፍ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ዓመታዊ የውይይት መድረክ ላይ ተገልጿል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ “የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የመድኃኒት አቅርቦት ስንሰለቱን ቀልጣፋና የአሠራር ስርዓቱን ግልጽ ለማድረግ ዲጂታላይዝድ የመድኃኒት አቅርቦት አሰራር እንዲኖረው የተጀመሩ በርካታ ሥራዎች ውጤታማ ሆኗል” ብለዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬሕይወት አበበ በበኩላቸው፣ በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የመድኃኒት ግዢ አዋጅ ወጥቶ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውሰው፤ አዋጁ በመቀየሩም የተራዘመ የግዢ ሂደትን ማስቀረት ተችሏል ብለዋል።

በቀጣይም የመድኃኒት ጥረትና ተደራሽነትን ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሠራ መመላከቱን ከጤና ሚኒስተር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በ2017 የበጀት ዓመት ከ68 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሠረታዊ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓት ተሰራጭቷል ተባለ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በ2017 የበጀት ዓመት ከ68 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሠረታዊ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓት ተሰራጭቷል ተባለ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0