ሩሲያ በፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያን በተመለከ አፍሪካ ያቀረበችውንና ቅድሚያ በተሰጣቸው ሌሎች ምክንያቶች የቆመውን ጥያቄ ትደግፋለች ሲሉ መልዕክተኛው ተናገሩ
20:14 18.10.2025 (የተሻሻለ: 20:24 18.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ በፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያን በተመለከ አፍሪካ ያቀረበችውንና ቅድሚያ በተሰጣቸው ሌሎች ምክንያቶች የቆመውን ጥያቄ ትደግፋለች ሲሉ መልዕክተኛው ተናገሩ
በተመድ የሩሲያ ቋሚ መልክተኛ ቫሲሊ ኔቤንዚያ እንደተናገሩት፤ የማሻሻያው ሂደት በተጋጩ ብሔራዊ ጥቅሞች እና በአምስት ቁልፍ የድርድር ስብስቦች ትስስር ምክንያት ተደናቅፏል።
⏱ ኔቤንዚያ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቃለ-ምልልስ እንዳብራሩት፣ በሁሉም ስብስቦች ላይ በአንድ ጊዜ ስምምነት ስለሚያስፈልግ፣ የጥያቄው ምላሽ ሂደት "በጣም የዘገየ" ሆኗል።
"አፍሪካን በተመለከተ፣ እኛ እንደ ሩሲያ እንዲሁም ሌሎቹም ብዙዎች በተመሳሳይ እንደሚሉት፣ በአፍሪካ ላይ የደረሰው ታሪካዊ ኢፍትሐዊነት መስተካከል አለበት። አፍሪካ በተሻሻለው የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በበቂ ሁኔታ መወከል አለባት" ሲሉ አረጋግጠዋል።
ኔቤንዚያ የአዳዲስ ምዕራባውያን አባላትን መጨመር ሞስኮ እንደምትቃወም በግልፅ በመግለጽ፣ ይልቁንም በአነስተኛ ውክልና ካለው የደቡብዊ ዓለም "በመጀመሪያ ደረጃ አፍሪካ፣ እስያ እና ላቲን አሜሪካ" ከፍተኛ ድምፅ እንዲኖራቸው ይገባል ብለው ሞግተዋል።
ዲፕሎማቱ የአፍሪካ የጋራ አቋም ለምክር ቤቱ ቋሚ መቀመጫ ያላትን ጥያቄ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል። በማሻሻያው ላይ ሁሉን አቀፍ ስምምነት ላይ ሲደረስ አፍሪካ "በተገቢው ሁኔታ እንደምትወከል" ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ንቤንዚያ የአፍሪካ አገራት በጋዛ ቀውስ ላይ የያዙትን አቋም አድንቀዋል።
"ይህ ግጭት ብዙ ሰላማዊ ዜጎችን ያለአግባብ ሕይወት እየቀጠፈ ስለሆነ፣ [የቅርብ ጊዜው] የተኩስ አቁም እንደሚዘልቅ ሁላችንም እየጸለይን ነው። ብዙ ሲቪሎች ሞተዋል" ብለዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X