https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት አገር በቀል አይደለም - የትምህርት አስተዳደር ባለሙያ
የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት አገር በቀል አይደለም - የትምህርት አስተዳደር ባለሙያ
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት አገር በቀል አይደለም - የትምህርት አስተዳደር ባለሙያ ለዘመናት የቆየው የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ከምዕራባውያን የተቀዳ በመሆኑ ኢትዮጵያዊ መልክ ይጎድለዋል ሲሉ ዶ/ር ሰለሞን በላይ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ። "ቀጥታ... 18.10.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-10-18T18:29+0300
2025-10-18T18:29+0300
2025-10-18T18:34+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07e9/0a/12/1929275_0:42:800:492_1920x0_80_0_0_83abe1b32fc8bb96947c3c685d002c77.jpg
የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት አገር በቀል አይደለም - የትምህርት አስተዳደር ባለሙያ ለዘመናት የቆየው የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ከምዕራባውያን የተቀዳ በመሆኑ ኢትዮጵያዊ መልክ ይጎድለዋል ሲሉ ዶ/ር ሰለሞን በላይ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ። "ቀጥታ የውጭውን ዓለም የሥርዓተ ትምህርት ከኢትዮጵያውያን ሕይወት ጋር ብዙም ግንኙነት የለውም፤ ልጆችን የማያሸጋግር፣ አካባቢውን የማይለውጥ፣ አካባቢውን ያልተገነዘበ ሥርዓተ ትምህርት ... ኢትዮጵያ አምጥተህ ስታስቀምጠው ግን አይገጣጠምም" ብለዋል። የትምህርት አስተዳደር ባለሙያው አክለውም፣ የኢትዮጵያ ልጆች የራሳቸው የሆነ ታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ሥነ ልቦና እና ባሕል ስላላቸው በሌላ አገር ዐውድ ውስጥ የተጻፈ ሥርዓተ ትምህርት አምጥቶ መጫን ልክ አለመሆኑን አስረድተዋል።"ቋንቋ ትልቁ እና በግልጽ የሚታየው የግንኙነታችን መስመር ነው፡፡ አሁን እንግዲህ ቋንቋ ስትወለድ ጀምሮ ያደክበት፣ የምታስብብበትና የምትናገረው ቋንቋ ተረስቶ በሌላ በባዕድ ቋንቋ መማር እና ማስተማራችን ሁሌም ይገርመኛል" በማለት ለአገር ውሰጥ ቋንቋ የተሰጠው ቦታ ማነሱን አስረድተዋል።በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2025
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07e9/0a/12/1929275_45:0:756:533_1920x0_80_0_0_cb9ba60f5c37e5f2f7d33eb17839dad6.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት አገር በቀል አይደለም - የትምህርት አስተዳደር ባለሙያ
18:29 18.10.2025 (የተሻሻለ: 18:34 18.10.2025) የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት አገር በቀል አይደለም - የትምህርት አስተዳደር ባለሙያ
ለዘመናት የቆየው የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ከምዕራባውያን የተቀዳ በመሆኑ ኢትዮጵያዊ መልክ ይጎድለዋል ሲሉ ዶ/ር ሰለሞን በላይ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።
"ቀጥታ የውጭውን ዓለም የሥርዓተ ትምህርት ከኢትዮጵያውያን ሕይወት ጋር ብዙም ግንኙነት የለውም፤ ልጆችን የማያሸጋግር፣ አካባቢውን የማይለውጥ፣ አካባቢውን ያልተገነዘበ ሥርዓተ ትምህርት ... ኢትዮጵያ አምጥተህ ስታስቀምጠው ግን አይገጣጠምም" ብለዋል።
የትምህርት አስተዳደር ባለሙያው አክለውም፣ የኢትዮጵያ ልጆች የራሳቸው የሆነ ታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ሥነ ልቦና እና ባሕል ስላላቸው በሌላ አገር ዐውድ ውስጥ የተጻፈ ሥርዓተ ትምህርት አምጥቶ መጫን ልክ አለመሆኑን አስረድተዋል።
"ቋንቋ ትልቁ እና በግልጽ የሚታየው የግንኙነታችን መስመር ነው፡፡ አሁን እንግዲህ ቋንቋ ስትወለድ ጀምሮ ያደክበት፣ የምታስብብበትና የምትናገረው ቋንቋ ተረስቶ በሌላ በባዕድ ቋንቋ መማር እና ማስተማራችን ሁሌም ይገርመኛል" በማለት ለአገር ውሰጥ ቋንቋ የተሰጠው ቦታ ማነሱን አስረድተዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X