አይኤምኤፍ በዚህ የ2025 ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ7.2 በመቶ ያድጋል ሲል ተነበየ
16:47 18.10.2025 (የተሻሻለ: 16:54 18.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አይኤምኤፍ በዚህ የ2025 ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ7.2 በመቶ ያድጋል ሲል ተነበየ
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ ትንበያ መሠረት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፍጥነት ከሚያድጉ ኢኮኖሚዎች መካከል አንዱ ሆኖ እንደሚቀጥል ይፋ አድርጓል።
ኢትዮጵያ የእድገት ትሩፋቶችን ለማስጠበቅ እና ማክሮ ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን ለማስቀጠል የአገር ውስጥ ገቢ ማሰባሰብን እና የዕዳ አስተዳደርን ማጠናከር እንደሚገባትም አሳስቧል፡፡
እነዚህ እርምጃዎች፣ የብድር ወጪን ለመቀነስ፣ ግልጽነትን ለማሻሻል እና ለአስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶች በቂ የገንዘብ ድጋፍን ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው።
ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ያቀረበቻቸው ምርቶች፣ ከውጭ የሚገኘው ዕርዳታ በመቀነሱና ዓለም አቀፍ የንግድ መስተጓጎል በመፈጠሩ ምክንያት የሚመጡትን አንዳንድ ጫናዎች ለማካካስ እገዛ ማድረጉንም ጨምሮ አመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X