በአፍሪካ እና በሩሲያ መካከል ያለው የጋራ ፈጠራ 'ታላቅ ዕድል' ነው ሲሉ ደቡብ አፍሪካዊው ባለሙያ ተናገሩ
15:29 18.10.2025 (የተሻሻለ: 15:44 18.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአፍሪካ እና በሩሲያ መካከል ያለው የጋራ ፈጠራ 'ታላቅ ዕድል' ነው ሲሉ ደቡብ አፍሪካዊው ባለሙያ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአፍሪካ እና በሩሲያ መካከል ያለው የጋራ ፈጠራ 'ታላቅ ዕድል' ነው ሲሉ ደቡብ አፍሪካዊው ባለሙያ ተናገሩ
"አፍሪካ እጅግ ብዙ ታሪኮች አሏት። ማንነታችን ውስጥ ያሉትን ውስብስብ እና ድንቅ ታሪኮቻችንን የምንናገርበት ጊዜ አሁን ነው" ሲሉ የ"ፍሪ ውመን ፊልምስ" ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጁዲ ንዎከዲ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
ንዎከዲ በሩሲያ እና በደቡብ አፍሪካ ፊልም ሰሪዎች መካከል ስላለው 'የእኔ አፍሪካ' የትብብር ፕሮጀክት ሲናገሩ፣ የሩሲያዊቷን ዳይሬክተር ኦልጋ አካቲየቫን “ሩሲያውያን የሚወዷት፣ ዘመናዊና ወቅታዊ የሆነች አፍሪካን የማስተዋወቅ” ራዕይ አድንቀዋል።
"ከአፍሪካ ጋር ወደፊት " በተሰኘው የአፍሪካ የባህል እና ሲኒማ ቀናት ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ጎን ለጎን በሁለቱ ቀጣናዎች መካከል እየጎለበተ የመጣውን የፈጠራ ትብብር አጉልተው አሳይተዋል።
"ሩሲያ-አፍሪካዊ እና አፍሪካ-ሩሲያዊ በሆኑ ታሪኮች ላይ በጋራ ፈጠራ እና በጋራ ስራ ላይ አብረን እንሰራለን። ይህ እኛ ልንመረምረው የሚገባ ታላቅ ዕድል ነው ብዬ አስባለሁ።"
ንዎከዲ በተጨማሪም የትክክለኛ ውክልና አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል፦
"አፍሪካን በተመለከተ ያለውን ነገር ማረም እና በጥንቃቄ ማቅረብ በጣም አስፈላጊ ነው... ዓለም አፍሪካን እንደ ድሃ ወይም ሙሰኛ አድርጎ ማየት ይወዳል። ብዙ ማኅበረሰቦች ግን ተመሳሳይ ተግዳሮቶች አሏቸው።"
ፍላጎት ላላቸው ፊልም ሰሪዎች ያላቸው መልዕክት አስመልክቶም፤
"ጥሩ ታሪኮችን እየፈለጋችሁ ከሆነ መገኘት ያለባችሁ አፍሪካ ውስጥ ነው" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
