ኢራን ከዚህ በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ምክንያት በሚጣሉ ገደቦች አትገደድም ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢራን ከዚህ በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ምክንያት በሚጣሉ ገደቦች አትገደድም ተባለ
ኢራን ከዚህ በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ምክንያት በሚጣሉ ገደቦች አትገደድም ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢራን ከዚህ በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ምክንያት በሚጣሉ ገደቦች አትገደድም ተባለ

  የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 2231 ጊዜው አልፏል፤ ይህም በኢራን ላይ ተጥለው የነበሩትን ሁሉንም የፀጥታው ምክር ቤት ገደቦች ያቋርጣል። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አባስ አራግቺ "ኢራን የኒውክሌር መስፋፋት መከላከያ ስምምነት ፈራሚ እንደመሆኗ፣ በቀጥታ በስምምነቱ ስር መሠረት ባሉ መብቶቿና ግዴታዎቿ ብቻ ትገደዳለች" ብለዋል።

አክለውም "ይህም በኒውክሌር መርሃ ግብሯ መጠን ላይ ምንም ዓይነት ገደብ አለመኖሩን፤ እንዲሁም ከዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር የሚደረግ ትብብርም በአጠቃላይ የጥበቃ ስምምነት ማዕቀፍ ውስጥና በኢራን ፓርላማ በቅርቡ በፀደቀው ሕግ መሠረት ብቻ መሆኑን ያጠቃልላል" ብለዋል።

እ.ኤ.አ. በ2015 የፀደቀው የተመድ የፀጥታው ምክር-ቤት ውሳኔ 2231፣ የጋራ ሁሉን አቀፍ የድርጊት መርሃ ግብር የኒውክሌር ስምምነት በዛሬው ዕለት ከጥቅም ውጭ ይሆናል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢራን ከዚህ በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ምክንያት በሚጣሉ ገደቦች አትገደድም ተባለ
ኢራን ከዚህ በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ምክንያት በሚጣሉ ገደቦች አትገደድም ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.10.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0