ኢትዮጵያ እና ቱርክ የገበያ ተደራሽነት ስምምነት ተፈራረሙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ እና ቱርክ የገበያ ተደራሽነት ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮጵያ እና ቱርክ የገበያ ተደራሽነት ስምምነት ተፈራረሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ቱርክ የገበያ ተደራሽነት ስምምነት ተፈራረሙ

ለኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ወሳኝ አካል የሆነውን ስምምነት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ፣ ከአፍሪካ የቱርክ የንግድ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ከቱርክ አቻቸው ፕሮፌሰር ሾማር ቦላት ጋር ተፈራርመዋል።

ሚኒስትሩ ይህ ለዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደታችን ትልቅ ምዕራፍ ነው ብለዋል። አክለውም ከሌሎች አባል አገራት ጋር የሚደረገው የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር ግማሹ በቴክኒክ ደረጃ መጠናቀቁን ጠቅሰው ከሌሎች ጋርም የድርድር ሂደቱ በተሳካ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።

የዓለም ንግድ ድርጅት 6ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ በቅርቡ ውጤታማ በሆነ ስኬት መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ለ7ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባም ዝግጅቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ የትስስሩ ገፁ አስነብቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ እና ቱርክ የገበያ ተደራሽነት ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮጵያ እና ቱርክ የገበያ ተደራሽነት ስምምነት ተፈራረሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.10.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0