ኢትዮጵያ እና ሕንድ የመጀመሪያውን የጋራ የመከላከያ ትብብር ስብሰባ በኒው ዴልሂ አካሄዱ
18:33 17.10.2025 (የተሻሻለ: 18:44 17.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ሕንድ የመጀመሪያውን የጋራ የመከላከያ ትብብር ስብሰባ በኒው ዴልሂ አካሄዱ
ስብሰባው በሕንድ የመከላከያ ሚኒስቴር አሚታብ ፕራሳድ እና በኢትዮጵያ የመከላከያ የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ የጋራ ሊቀ -መንበርነት ተመርቷል።
ሁለቱ ወገኖች በመካሄድ ላይ ያለውን የመከላከያ ትብብር ገምግመው፦
በሥልጠና፣
በጋራ ወታደራዊ ልምምዶች፣
በሕክምና ትብብር እና
በመከላከያ ኢንዱስትሪ ተሳትፎ ዙሪያ ለአዲስ ትብብር የሚሆኑ መንገዶችን ተወያይተዋል።
ሁለቱም ልዑካን ቡድኖች የመከላከያ ትብብር እንቅስቃሴዎችን የበለጠ ለማሳደግ እና ለማስፋት መስማማታቸውን የሕንድ መንግሥት የፕሬስ ኢንፎሜሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
