በትግራይ እና አፋር ክልሎች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከ43 ሺህ በላይ ሰዎች ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበትግራይ እና አፋር ክልሎች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከ43 ሺህ በላይ ሰዎች ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ
በትግራይ እና አፋር ክልሎች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከ43 ሺህ በላይ ሰዎች ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.10.2025
ሰብስክራይብ

በትግራይ እና አፋር ክልሎች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከ43 ሺህ በላይ ሰዎች ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ

ጥቅምት 1 ቀን በተከሰተው የ5.7 መጠነ ልኬት የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ አንዲት ሕጻን ሕይወቷ ሲያልፍ በዘጠኝ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአፋር ክልል በርሃሌ ወረዳን ጠቅሶ የአገር ውስጥ ሚዲያ አስታውሷል።

የአፋር ክልል እንዳስታወቀው፦

ከ1 ሺህ 400 በላይ ቤቶች፣

12 ትምህርት ቤቶች፣

12 የጤና ጣቢያዎች እና

ከ150 በላይ የውሃ ማጠራቀሚያዎች ወድመዋል፡፡

የትግራይ አደጋ ስጋት አመራር ቢሮ በበኩሉ፦

በመቀሌ ከተማ አቅራቢያ 40 መኖሪያ ቤቶች መፈራረሳቸ እና

ከ225 በላይ ነዋሪዎች መኖሪያ አልባ መሆናቸውን አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር እና የሚያስፈልገውን የእርዳታ መጠን ለመወሰን የግምገማ ቡድኖችን ወደ ስፍራው ማሰማራቱ ተዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0