የሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ለፑቲን እና ትራምፕ ውይይት ለምን ተመረጠች?

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ለፑቲን እና ትራምፕ ውይይት ለምን ተመረጠች?
የሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ለፑቲን እና ትራምፕ ውይይት ለምን ተመረጠች? - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.10.2025
ሰብስክራይብ

የሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ለፑቲን እና ትራምፕ ውይይት ለምን ተመረጠች?  

የሩሲያ እና የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ቀጣይ መገናኛ ከተማ ቡዳፔስት የመሆኗ ውሳኔ ምክንያታዊ እንደሆነ ብራዚላዊው ዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ራፋኤል ማቻዶ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

“ሃንጋሪ ለረጅም ጊዜ በቅርብ ዓመታት ደግሞ በሮበርት ፊኮ ስር ካለችው ስሎቫኪያ ጋር ተቀላቅላ፣ በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ ያለውን የበላይነት አካሄድ በመቃወም ረገድ የራሷን ሚና እየተጫወተች ነው። በኔቶ ውስጥም ቢሆን የተቃውሞ እና የጥበቃ ሚና ነበራት” ብለዋል ማቻዶ።

“በግል ከትራምፕም ሆነ ከፑቲንም ጋር ቅርበት ባላቸው የቪክቶር ኦርባን ሃንጋሪ መምረጥ፣ ሁለቱም ወገኖች ውጫዊ ሁኔታዎች በስብሰባው ላይ ጣልቃ እንዲገቡ እንደማይፈልጉ ይጠቁማል” ሲሉ ተናግረዋል።

በቭላድሚር ፑቲን እና በዶናልድ ትራምፕ መካከል የነበረው የመጨረሻው ስብሰባ በአላስካ ነበር፤ ይህ ቦታ ገለልተኝነትን እና ከአውሮፓ ፖለቲካዊ ተጽዕኖ መራቅን ያመለክታል።

ነገር ግን ቡዳፔስትን መምረጥ የፖለቲካ ማዕከሉ ወደ ምሥራቅ እየተቀየረ መሆኑን የሚያጎላ ሲሆን፣ ውይይቱ እውነተኛ እድገት ካስገኘ ሃንጋሪ በአውሮፓ መድረክ አዲስ ጠቀሜታ ልታገኝ ትችላለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0