ቡርኪና ፋሶ ለቀድሞ መሪዋ ቶማስ ሳንካራ መታሰቢያ ወርሃዊ ወታደራዊ ሥነ-ሥርዓት አወጀች
13:44 17.10.2025 (የተሻሻለ: 13:54 17.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቡርኪና ፋሶ ለቀድሞ መሪዋ ቶማስ ሳንካራ መታሰቢያ ወርሃዊ ወታደራዊ ሥነ-ሥርዓት አወጀች
ጠቅላይ ሚንስትር ሪምታልባ ዣን ኢማኑኤል ኡዴድራጎ የሳንካራን ግድያ 38ኛ ዓመት መታሰቢያን አስመልክቶ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ እንዳስታወቁት፣ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ለሳንካራ ክብር የሚሰጥ ወርሃዊ የማስታወሻ ሥነ-ሥርዓት በእያንዳንዱ ወር የመጀመሪያ ሐሙስ ቀን 10 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።
ዝግጅቱ የቡርኪና ፋሶን አብዮታዊ መሪ ተሞክሮ ለማክበር ወታደራዊ ሠራተኞችን፣ ዜጎችን እና ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን በአንድነት ያሰባስባል።
መርሃ ግብሩ የሚከተሉትን ዝግጅቶች ያካትታል፦
የጥበቃ ለውጥ፣
በአብዮታዊ ዩኒፎርም የሚደረግ ሰልፍ፣
የፈረስ ጉግስ ሥነ-ሥርዓት እና
የአበባ ጉንጉን የማኖር ሥነ-ሥርዓት ይገኙበታል።
ሁሉም እንቅስቃሴዎች የሚካሄዱት ኦጋዱጉ በሚገኘውና ባለፈው ግንቦት ወር በተመረቀው፣ የሳንካራ እና የ12 አጋሮቻቸው አስከሬን ባረፈበት፣ እንደ ብሔራዊ የማስታወሻ ምልክት ሆኖ በቆመው ቶማስ ሳንካራ መታሰቢያ ስፍራ ላይ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
