የቻድ ፕሬዝዳንት ሽብርተኝነት ላይ ድል ለምቀዳጀት ዓለም አቀፍ ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ
20:11 16.10.2025 (የተሻሻለ: 20:14 16.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቻድ ፕሬዝዳንት ሽብርተኝነት ላይ ድል ለምቀዳጀት ዓለም አቀፍ ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ
ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ በሮም በተካሄደው ዓለም አቀፉ የአቃባ የሽብርተኝነት መከላከል የመሪዎች ስብሰባ ላይ ለጸጥታ ስጋቶች የጋራ አካሄድ እንዲኖር አሳስበዋል።
"በሽብርተኝነት፣ በተደራጁ ወንጀሎች እና በሕገወጥ ስደት ላይ የምንቀዳጀው ድል የሚገኘው በጦር ሜዳ ብቻ አይደለም" ሲሉ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ ትግሉ "በትምህርት ቤቶች፣ በገጠር እና ተስፋቸውን ባጡ የወጣቶች ማዕከላትም ውስጥ ይካሄዳል" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንቱ የአክራሪነትን መንስኤዎች ለመቅረፍ ልማትን ከጸጥታ ስትራቴጂዎች ጋር ማዋሃድ አስፈላጊ መሆኑን አበክረው ገልጸዋል።
ይህንንም ለማሳካት "ቻድ ኮኔክሽን 2030" የተሰኘውን ብሔራዊ የልማት እቅድ ያቀረቡት ማሃማት፣ ይህ ፕሮጀክት የተረጋጋና ሁሉን አቀፍ የወደፊት ሕይወትን ለመገንባት በፈጠራ፣ በመልካም አስተዳደር፣ በመሠረተ ልማት እና በወጣቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን አስታውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X