ትራምፕ ስለ ቶማሃውክ ሚሳኤል የሰጡት አስተያየት በአላስካ የተደረገው ውይይት ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም - ላቭሮቭ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱትራምፕ ስለ ቶማሃውክ ሚሳኤል የሰጡት አስተያየት በአላስካ የተደረገው ውይይት ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም - ላቭሮቭ
ትራምፕ ስለ ቶማሃውክ ሚሳኤል የሰጡት አስተያየት በአላስካ የተደረገው ውይይት ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም - ላቭሮቭ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.10.2025
ሰብስክራይብ

ትራምፕ ስለ ቶማሃውክ ሚሳኤል የሰጡት አስተያየት በአላስካ የተደረገው ውይይት ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም - ላቭሮቭ

“ስለ ቶማሃውክ የተናገሩት አንዳችም ነገር በአላስካ በሃሳብ ደረጃ የተወያየነው ጉዳይ ላይ ተጽዕኖ የለውም፤ በሃሳብም በተግባርም ደረጃ ብል ይቀላል” ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል።

ሌሎች ያነሷቸው ሀሳቦች፦

▪ ሩሲያ ለአላስካው ውይይት ውጤት የአሜሪካን ተጨባጭ ምላሽ አሁንም እየጠበቀች ነው።

▪ ሞስኮ በአላስካው ጉባኤ ላይ በተገኘው ስምምነት ላይ በመመስረት በተለያዩ ደረጃዎች ከዋሽንግተን ጋር ተግባራዊ ጉዳዮችን በማንኛውም ጊዜ ለመወያየት ዝግጁ ነች።

▪ ለዩክሬን የሚደረጉ የቶማሃውክ አቅርቦቶች የሩሲያ-አሜሪካ ግንኙነትን መደበኛ ለማድረግ በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ከፍተኛ ስጋት ይደቅናሉ።

▪ ኪዬቭ በሩሲያ ግዛት ላይ ለሰነዘረቻቸው ጥቃቶች አሜሪካ መረጃ እንዳቀረበች የሚገልጹ የፋይናንሻል ታይምስ ዘገባዎችን ሩሲያ ተመልክታለች፤ በዚህም ሞስኮ ከዋሽንግተን ማብራሪያ ጠይቃለች።

▪ በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው የሥራ ግንኙነት በተለያዩ መንገዶች ቀጥሏል፤ ነገር ግን እስካሁን ምንም ከፍተኛ ደረጃ ስብሰባዎች አልታቀዱም።

▪ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ኪዝ ኬሎግ በዩክሬን ያለው ግጭት “እንዲያበቃ” ጥሪ አቅርበዋል።

▪ የትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ምክንያታዊ ሰው ናቸው፤ በመካከለኛው ምስራቅ ያሳዩትን አቅም በዩክሬን ቢደግሙት ሞስኮ በደስታ ትቀበላለች።

▪ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባለቤት በዩክሬን ግጭት ውስጥ በተለይም ልጆችን ከመመለስ ጋር በተያያዘ ጠቃሚ ሚና ይጫወታሉ።

▪ ሩሲያ በዩክሬን የኢስታንቡል ሂደት ላይ ባቀረበችው ማሻሻያ ሀሳብ ዙሪያ ምላሽ እየጠበቀች ነው፤ እስካሁን ከዝምታ ውጪ ምንም የለም።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0