አዲስ አሸባሪ ቡድን ከናይጄሪያው ቦኮ ሃራም እንደተገነጠለ ተነገረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአዲስ አሸባሪ ቡድን ከናይጄሪያው ቦኮ ሃራም እንደተገነጠለ ተነገረ
አዲስ አሸባሪ ቡድን ከናይጄሪያው ቦኮ ሃራም እንደተገነጠለ ተነገረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.10.2025
ሰብስክራይብ

አዲስ አሸባሪ ቡድን ከናይጄሪያው ቦኮ ሃራም እንደተገነጠለ ተነገረ

"ይህ አዲስ የዉሉዉሉ ቡድን ከቦኮ ሃራም በመገንጠል በሰሜን ማዕከላዊ ዞን ብቅ ማለት ጀምሯል፡፡ የላኩራዋ ቡድን አሁን በኳራ ትልቅ ችግር ሆኗል" ሲሉ የናሳራዋ ግዛት ገዥ አብዱላሂ ሱሌን ጠቅሶ የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

የግዛቱ አስተዳዳሪ፤ ከአዲሱ አሸባሪ ቡድን የተውጣጡ ታጣቂዎች በሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያ መኖራቸውን የደህንነት መረጃዎችን በመጥቀስ ገልጸዋል፡፡ ይህ ክልል የቤኑዌ፣ ኮጊ፣ ኳራ፣ ናሳራዋ፣ ኒጀር፣ ፕላቶ ግዛቶችን እና የናይጄሪያ ዋና ከተማ አቡጃን ጨምሮ የፌደራል ዋና ከተማ ግዛትን ያካትታል።

ቡድኑ ወደ ግዛታቸው ሰርጎ እንዳይገባ የደህንነት ባለሥልጣናት እንዲከላከሉ አብዱላሂ ሱሌ ጥሪ አቅርበዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0