የባሕርተኞች ሥልጠናን ወደ ቴክኒክ እና ሙያ የትምህርት ተቋማት ለማስፋት እየሠራን ነው - የኢትዮጵያ ማሪታይም ማሠልጠኛ ተቋም

ሰብስክራይብ

የባሕርተኞች ሥልጠናን ወደ ቴክኒክ እና ሙያ የትምህርት ተቋማት ለማስፋት እየሠራን ነው - የኢትዮጵያ ማሪታይም ማሠልጠኛ ተቋም

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍራንስ ጁበርት፤ ኢትዮጵያ ለሌሎች ወደብ አልባ የዓለም ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ጠንካራ የባሕርተኞች ሥልጠና አደረጃጀት ባለቤት መሆኗን ተናግረዋል።

ኃላፊው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ተቋሙ ከ29 ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ተቀብሎ በማሠልጠን ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

"ከ7 ሺህ በላይ ባሕርተኞች አሉን። ከ2 ሺህ 600 በላይ መኮንኖችን ያሠለጠንን ሲሆን፤ በዓመት የምናሠለጥናቸውን የመሐንዲሶች ቁጥርም 1ሺህ ለማድረስ እየሠራን ነው" ብለዋል።

ፍራንስ ጁበርት የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄዱ በሀገሪቱ ዘርፉን ይበልጥ ለማስፋት ያለውን አስተዋጽኦሞ አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0