ኢትዮጵያ የንጋት ሐይቅን በፍኖተ ካርታ ለመምራት ሂደት ላይ መሆኗ ተገለፀ
18:57 15.10.2025 (የተሻሻለ: 19:04 15.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የንጋት ሐይቅን በፍኖተ ካርታ ለመምራት ሂደት ላይ መሆኗ ተገለፀ
በግድቡ ላይ የተፈጠረውና ከአፍሪካ 4ኛው ግዙፍ ሀይቅ የሆነው የንጋት ሰው ሠራሽ ሀይቅን የዘላቂ ልማት ማዕከል የሚያደረግ ስትራቴጂክ እቅድ ወደ ተግባር ለማስገባት ያለመ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ፍኖተ ካርታውን ከባለድርሻ አካላት ጋር ከሚደረጉ ውይይቶች በሚገኙ ግብዓቶች በማዳበር ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ፣ ውሃውን በቋሚነት ለማስተዳደርና ቅንጅታዊ አሠራርን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሠራ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
በመድረኩ ባደረጉት “የንጋት ሀይቅ ለቀጣዩ ትውልድ በቅብብሎሽ የምናስረክበው ትልቅ በረከት ነው” ብለዋል።
ለሐይቁ የተዘጋጀው ማስተር ፕላን በውስጡ ምን ይዟል፦
የኢኮ ቱሪዝም አገልግሎት፣
የዓሣ ንግድ ማስፋት፣
ለግብርና ዘመናዊ መስኖ አቅም መፈጠር፣
አዳዲስ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን የሚያጎለብትበት ቀጣይ ስራዎችን ያመላክታል፡፡
የአፈፃፀም ስትራቴጂውን ለማጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለሚደረግ ውይይት ረቂቅ ዕቅዱ አሁንም ክፍት እንደሆነ መናገራቸውን የዘገበው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X