የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት የማስፋት ቁርጠኝነት አብነት ማድረግ ይገባል - የአፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ ጥምረት
18:34 15.10.2025 (የተሻሻለ: 18:44 15.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት የማስፋት ቁርጠኝነት አብነት ማድረግ ይገባል - የአፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ ጥምረት
ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ሥርዓት ለመሸጋገር መሠረተ ልማት ሥራ ላይ በትኩረት እየሠራች እንደምትገኝ የጥምረቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዋረን ኦንዳንጄ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
"የኢትዮ ቴሌኮምን የሕዝብ የመኪና መሙያ ማዕከላት ተመልክቻለሁ። በሥፍራዎቹ ቻርጅ ለማድረግ የተሰለፉ ተሸከርካሪዎችም ሽግግሩ በሂደት ላይ መሆኑን ይናገራሉ። መሠረተ ልማቱን በመላ ሀገሪቱ ለማዳረስ ይበልጥ መሥራት ይገባል" ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዘርፉ እያሳየችው ያለው ቁርጠኝነት ኢንቨስትመንትን ከመሳብ አንጻር ያለውን አንደምታም አንስተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X