የባሕር ሳይንስን ለመማር ከሀገር መውጣት ግዴታ አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ዘመናዊ የሥልጠና ሥርዓት መዘርጋት ይገባል - ካፒቴን ሳሙኤል ሲሳይ
17:46 15.10.2025 (የተሻሻለ: 17:54 15.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የባሕር ሳይንስን ለመማር ከሀገር መውጣት ግዴታ አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ዘመናዊ የሥልጠና ሥርዓት መዘርጋት ይገባል - ካፒቴን ሳሙኤል ሲሳይ
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፓርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ካፒቴኑ፤ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የባሕር ኢንዱስትሪው በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለበትን የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ ጉልህ ሚና መጫወት እንደሚችሉ ይገልጻሉ።
"እዚህ ጉባኤ ላይ የተገኙት ግዙፍ የመርከብ እና የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ከፍተኛ የሰው ኃይል እጥረት አለባቸው። የወጣቶች ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ ይህን ክፍተት የመሙላት እምቅ አቅም አላት" ብለዋል።
ካፒቴኑ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ ኢትዮጵያ ከዘርፉ ዓለም አቀፍ ተዋንያን ጋር በትብብር ሥልጠናዋን ማላቅዋ የሚፈጥረውን ዕድልም አንስተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X