አዲሱ የማዳጋስካር አስተዳደር ቁልፍ ሰዎች እነማን ናቸው?

አዲሱ የማዳጋስካር አስተዳደር ቁልፍ ሰዎች እነማን ናቸው?
ሚካኤል ራንድሪያኒሪና፣ ጊዜያዊ መሪ፦
በአንትሲራቤ ወታደራዊ አካዳሚ የሰለጠኑት ኮሎኔሉ፤ ልዩ የተቋማዊ ጥበቃ ድጋፍ ሰጪ ወታደራዊ ክፍል (ካፕሳት) አዛዥ ነበሩ፤
ትልቋ የደቡባዊ ማዳጋስካር ከተማ በሆነችው በቶሊያራ የቀድሞ የእግረኛ ጦር አዛዥ የነበሩ ሲሆን በርካታ ጦር ሰፈሮችንም በአዛዥነር መርተዋል፤
ለመንግሥት ባላቸው ትችታዊ አቋም ይታወቃሉ፤
በዓመፅ ቀስቃሽነት ክስ ከህዳር 2023 - የካቲት 2024 ታስረው ወደ ሥራቸው ተመልሰዋል፤
መነሻቸው በሆነው አንድሮ ክልል ከ2016 እስከ 2018 ገዥ ሆነው አገልግለዋል።
ዴሞስቴኔ ፒኩላስ፣ የጦር ኃይሎች አዲሱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም፦
እስከ 2021 ድረስ በአምቦአሳሪ አትሲሞ የባለብዙ ተልዕኮ ሻለቃን በአዛዥነት ያገለገሉ ሲሆን የድርቅና ረሃብ እርዳታ የኦፕሬሽን ማስተባበሪያ ማዕከልን መርተዋል፤
ከ2019 እስከ 2023 በአንትሲራቤ ወታደራዊ አካዳሚን መርተዋል፣ በተለይም ከቻይና እና ከፈረንሳይ ጋር በወታደራዊ ትብብር ፕሮግራሞች ላይ ተሳትፈዋል፤
የካፕሳት ወታደራዊ ክፍል በማዳጋስካር ፕሬዝዳንት ላይ በተነሱ ተቃውሞዎች ምክንያት ሥልጣን ከያዘ በኋላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው ተሹመዋል፤
በሜላኪ ክልል ማይንቲራኖ የተወለዱት ግለሰቡ የግሪክ እና የማዳጋስካር የዘር-ግንድ አላቸው።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
