የብራዚል ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያከናወነቻቸውን ሥራዎች አደነቁ
20:10 14.10.2025 (የተሻሻለ: 20:14 14.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የብራዚል ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያከናወነቻቸውን ሥራዎች አደነቁ
የሀገሪቱ የግብርናው ዘርፍ ኢኒሼቲቮች አበረታች መሆናቸውን ሉላ ዳሲልቫ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በጣልያን ሮም እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም የምግብ ፎረም ጎን ለጎን በተካሄደው 2ኛው የግሎባል አሊያንስ ኢኒሼቲቭ የሀገራት ትብብር መድረክ ላይ ነው፡፡
በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ በበኩላቸው፤ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት መገኘት መቻሉን አንስተዋል፡፡
ለዚህም የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርን በማሳያነት በመጥቀስ፤ የእንቁላል፣ ወተት፣ ማርና ዓሣ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር መደረጉን አብራርተዋል፡፡
በ2024 በብራዚል የተጀመረው ግሎባል አሊያንስ ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያ ጨምሮ በርካታ ሀገራትን ያቀፈ የትብብር ጥምረት ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X