የሻርም ኤል ሼክ የሰላም ጉባኤ ኔታንያሁን ከአደጋ ያወጣ ነው - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሻርም ኤል ሼክ የሰላም ጉባኤ ኔታንያሁን ከአደጋ ያወጣ ነው - ባለሙያ
የሻርም ኤል ሼክ የሰላም ጉባኤ ኔታንያሁን ከአደጋ ያወጣ ነው - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.10.2025
ሰብስክራይብ

የሻርም ኤል ሼክ የሰላም ጉባኤ ኔታንያሁን ከአደጋ ያወጣ ነው - ባለሙያ

በአልጄሪያ አም ሲላ መሐመድ ቡዲያፍ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት አህመድ ሩዋጅያ፤ ጉባኤው "ለእስራኤል መንግሥት ቀደም ሲል መደበኛ ግንኙነትን ይደግፉ ከነበሩ የአረብ ሀገራት ዳግም የመገናኘት እድልን የሰጠ ነው” ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ፤ "ይህን ግንኙነት የሚፈልጉት ሀገራትም ቢሆኑ ታላቋን እስራኤልን የማስፋፋት፣ ማለትም አብዛኞቹን የአረብ ሀገራት የመዋጥ ዕቅዱን ባልተወው የእስራኤል መንግሥት ስጋት ውስጥ በመሆናቸው መደበኛ ግንኙነቱ አይሳካም" ብለው እንደሚያምኑ ባለሙያው ጠቁመዋል።

ሩዋጅያ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል በአሸማጋዮች አማካኝነት የተደረሰውን “ተሰባሪ” ስምምነት "ፍፁም እርግጠኛ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ የተንጠለጠለ" ሲሉ ገልጸውታል።

ሆኖም ስምምነቱ ለፍልስጤም ሕዝብ "እረፍት" እና "ትንሽ ተስፋ" ይሰጣል በማለት አጠቃለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0