ኢትዮጵያ የባሕር መሀንዲሶችን አሠልጥና ለውጭ ገበያ እያቀረበች እንደምትገኝ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የባሕር መሀንዲሶችን አሠልጥና ለውጭ ገበያ እያቀረበች እንደምትገኝ ተገለፀ
ኢትዮጵያ የባሕር መሀንዲሶችን አሠልጥና ለውጭ ገበያ እያቀረበች እንደምትገኝ ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የባሕር መሀንዲሶችን አሠልጥና ለውጭ ገበያ እያቀረበች እንደምትገኝ ተገለፀ

በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሠልጥነው በውጪ ሀገራት ከተቀጠሩት ኢትዮጵያውያን የማሪታይም ምሩቃን መካከል፤ 26ቱ በዓለም ትልልቅ የዘርፉ ተቋማት በከፍተኛ ኃላፊነት፣ አማካሪነት እና ባለሞያነት እየሠሩ እንደሆነ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ተቋሙ ከሀገሪቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሜካኒካል እና ኤሌክትሪካል ምህንድስና የተመረቁ ምሩቃንን መልምሎ ለ6 እና ለ9 ወራት በማሠልጠን የማሪታይም ዘርፍ ባለሞያዎችን እያበቃ ይገኛል ማለታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

የማሪታይም መሀንዲሶቹ ከውጪ ሀገራት በመጡ መምህራን ዓለም አቀፍ መስፈርት ያሟላ ሥልጠና እንደሚሰጣቸው ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል። ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ይህንን ሥራ ከጀመረ 12 ዓመታት አስቆጥሯልም ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0