የማዳጋስካር ከፍተኛ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ከወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ የጦር ሠራዊት ኮሎኔል በፕሬዝዳንትነት ሀገሪቱን እንዲመሩ ጥሪ አቀረበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየማዳጋስካር ከፍተኛ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ከወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ የጦር ሠራዊት ኮሎኔል በፕሬዝዳንትነት ሀገሪቱን እንዲመሩ ጥሪ አቀረበ
የማዳጋስካር ከፍተኛ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ከወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ የጦር ሠራዊት ኮሎኔል በፕሬዝዳንትነት ሀገሪቱን እንዲመሩ ጥሪ አቀረበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.10.2025
ሰብስክራይብ

የማዳጋስካር ከፍተኛ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ከወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ የጦር ሠራዊት ኮሎኔል በፕሬዝዳንትነት ሀገሪቱን እንዲመሩ ጥሪ አቀረበ

በማዳጋስካር ስላለው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች፦

🟠 ወታደራዊ ኃይሉ የብሔራዊ ምክር ቤቱ፤ ፕሬዝዳንት ራጆሊናን ለመክሰስ ድምጽ ከሰጠ በኋላ ሥልጣን መያዙን አስታውቋል።

🟠 የሀገሪቱ ልዩ ወታደራዊ ክፍል (ካፕሳት) ተግባራዊ የሚደረጉ እርምጃዎችን ዘርዝሯል፦

የሴኔት እና የከፍተኛ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ፈርሷል፤ የብሔራዊ ምክር ቤቱ ግን እንደተጠበቀ ነው።

ሕገ-መንግሥቱ ተሽሯል፤ ለአዲስ ሕገ-መንግሥት ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል።

አዲስ መንግሥት ከመመሥረቱ በፊት አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሾማል።

እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ የሽግግር ወቅት።

🟠የሀገሪቱ የሕግ አስከባሪ ኃይል እና ሠራዊቱ የማዳካስካር ፕሬዝዳንትነት ኃላፊነትን በጋራ ይቆጣጠራሉ።

ምክር ቤቱ ከሠራዊት፣ ከሕግ አስከባሪ ኃይሉ እና ከብሔራዊ ፖሊስ የተውጣጡ መኮንኖችን ያቀፈ ይሆናል ሲሉ የካፕሳት ኃላፊ ኮሎኔል ሚካኤል ራንድሪያኒሪና ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

የከፍተኛ ሲቪል አማካሪዎች ተሳትፎ አይገለልም።

🟠 የብሔራዊ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ራጆሊናን ከሥልጣን ለማውረድ ድምጽ ከሰጠ በኋላ በቅርብ ቀናት ውስጥ የሲቪል መንግሥት እንደሚመሠረት ኮሎኔል ራንድሪያኒሪና ማክሰኞ ዕለት ከፕሬዝዳንታዊ መኖሪያ ቤት አምቦትሲሮሂትራ ቤተ-መንግሥት ሆነው ተናግረዋል።

🟠 ራጆሊና ሰኞ ዕለት ሀገሪቱን ለቀው የወጡ ሲሆን ከሀገር ውጭ ከማይታወቅ ስፍራ ሆነው ባደረጉት ንግግር ሥልጣን ለመልቀቅ አሻፈረኝ ብለው ነበር።

🟠 የፓርላማ አባላት እሳቸውን ለመክሰስ ድምፅ ለመስጠት ሲዘጋጁ ራጆሊና ማክሰኞ ዕለት የብሔራዊ ምክር ቤቱን መፍረስ አወጁ።

🟠 ልዩ ወታደራዊ ክፍሉ (ካፕሳት) በ2009 አንድሪ ራጆኤሊና ወደ ሥልጣን እንዲመጡ ደግፏል። በወቅቱ የቀድሞው ፕሬዝዳንት የአሁኑ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ማርክ ራቫሎማናና የተቃዋሚ መሪ ነበሩ።

🟠 መስከረም 25 ቀን በውሃና በኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በሂደት የፕሬዝዳንቱን ሥልጣን መልቀቅ ወደመጠየቅ ተሸጋግሯል።

🟠 በኬንያ እና ኔፓል የአዲሱ ትውልድ "ጀነሬሽን ዜድ" እንቅስቃሴዎች ተነሳስተው፤ ከተቃውሞዎቹ ጀርባ ያሉት ወጣቶች ድህነትንና ሙስናን አውግዘዋል።

🟠በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሠረት በተቃውሞዎቹ ቢያንስ 22 ሰዎችን ሲገድሉ ከመቶ በላይ ሰዎች ቆስለዋል። የማዳጋስካር መንግሥት ይህን ቁጥር በመቃወም 12 ሰዎች ብቻ መሞታቸውን ተናግሯል።

🟠 የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ፤ "ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በመጣስ ከተደራጀ ስብሰባ የሚመጣ ማንኛውም ውሳኔ" "ባዶ እና ከንቱ" እድርጎ እንደሚቆጥረው አስጠንቅቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0