የኢትዮጵያ እምቅ የታዳሽ ኃይል ሀብት በአረንጓዴ ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ መነቃቃትን ፈጥሯል - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር
18:18 14.10.2025 (የተሻሻለ: 18:24 14.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ እምቅ የታዳሽ ኃይል ሀብት በአረንጓዴ ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ መነቃቃትን ፈጥሯል - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር
ሀገሪቱ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ዘርፍን በፖሊሲ እና ስትራቴጂ በመደገፍ ውጤታማ ሥራዎችን እያከናወነች ትገኛለች ያሉት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሐሰን ናቸው፡፡
◻ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን በስፋት ለማምረት የሚያስችል የተፈጥሮ ማዕድናት እንዳሏት፣
◻ የተለያዩ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያዎች በዘርፉ ለመሠማራት እንቅስቃሴ እንደጀመሩ፣
◻ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን የተለያዩ ሀገራት ኩባንያዎች እየሳበ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ አማራጭ የታዳሽ ኃይል አቅርቦት ያላት ሀገር መሆኗን ለማሳየት በአዲስ አበባ የሚካሄደውን “አፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ 2025” የተሰኘ አህጉራዊ ኹነት በአዳማ አንድ የንፋስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ የማስተዋወቅ ሥራ ተከናውኗል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X