አፍሪካ የባሕር ላይ የወደፊት እጣ ፈንታዋን መምራት አለባት - የኢትዮጵያ የማሪታይም ባለሥልጣን

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ የባሕር ላይ የወደፊት እጣ ፈንታዋን መምራት አለባት - የኢትዮጵያ የማሪታይም ባለሥልጣን
አፍሪካ የባሕር ላይ የወደፊት እጣ ፈንታዋን መምራት አለባት - የኢትዮጵያ የማሪታይም ባለሥልጣን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.10.2025
ሰብስክራይብ

አፍሪካ የባሕር ላይ የወደፊት እጣ ፈንታዋን መምራት አለባት - የኢትዮጵያ የማሪታይም ባለሥልጣን

"እኛ አፍሪካውያን ትልቅ አቅም አለን...በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥሩ የባሕር ላይ ሠራተኞች አቅራቢ መሆን እንችላለን። ስለተሳትፎ ብቻ አይደለም፤ መሪ መሆን አለብን፤ በአፍሪካዊነት መሳተፍ አለብን" ሲሉ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍራኦል ጣፋ ከአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ማሪታይም "የማይታይ መሠረተ ልማት" መሆኑን አጽንኦት የሰጡት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ለአፍሪካ የሎጂስቲክስና የንግድ ኮሪደሮች መሠረት ነውም ብለዋል። ኢትዮጵያ የባሕር በር ባይኖራትም በንቃት የባሕር ላይ ሠራተኞችን እያሰለጠነች እና የሰማያዊ ኢኮኖሚ አቅሟን እያሰፋች መሆኑን ገልጸዋል።

ከ7 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ የማሪታይም ሠራተኞች በዓለም አቀፍ መርከቦች ላይ እየሠሩ ሲሆን የሥልጠና ፕሮግራሞችንም በመጨመር ኢትዮጵያ አህጉራዊ አቅሟን ወደ ቀጣናዊ ጥንካሬ በመቀየር ራሷን የወደፊት የማሪታይምና የሎጂስቲክስ ማዕከል አድርጋ ለማስቀመጥ አልማለች፡፡

በሰው ሠራሽ አሰተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0