ዛምቢያ በማር ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መሥራት እንደምትሻ ገለፀች
17:04 14.10.2025 (የተሻሻለ: 17:14 14.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዛምቢያ በማር ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መሥራት እንደምትሻ ገለፀች
የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የኢትዮጵያ እና ዛምቢያን የማር ገበያ ሰንሰለት ትብብር ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት በደቡብ ማዕከላዊ አፍሪካዊቷ ሀገር አዘጋጅቷል፡፡
በዚህ ወቅት ዛምቢያ ከአትዮጵያ ጋር እንደ ንብ ዘረመል፣ የበሽታ ቁጥጥር፣ የወጪ ንግድ ማረጋገጫ እና የንብ ቀፎ አስተዳደር ባሉ ዘርፎች የቴክኒክ ትብብር እንደምትሻ የሀገሪቱ የአረንጓዴ ኢኮኖሚና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር ተጠባባቂ ቋሚ ፀሐፊ ራንፎርድ ሲሙምብዌ ገልፀዋል።
“ይህ ግንኙነት በደን ልማት እና ዘላቂ የግብርና እሴት ሰንሰለቶች፣ በተለይም በማር ዘርፍ ትብብርን ለማጠናከር እድል ይሰጣል” ብለዋል።
በኢትዮጵያ የዛምቢያ ተጠባባቂ አምባሳደር ቶም ሚሼሎ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ከ326 ሺህ ቶን በላይ ማር ማምረት እና በአረንጓዴ አሻራ ከ2011 ጀምሮ 40 ቢሊየን በላይ ዛፎችን መትከል እንደቻለች በማንሳት እውቅና ሰጥተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን መሪ እና የግብርና ሚኒስቴር አማካሪ ግርማ ሙሉጌታ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል በዘላቂ እና ደን ላይ የተመሠረቱ ኢንተርፕራይዞች በተለይም በማር እሴት ሰንሰለት ዙሪያ የጋራ ፍላጎት እንዳለ ጠቁመዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X