ኢትዮጵያ የመልማት መብቷን በየትኛውም አይነት ጫና አታቆምም - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
13:07 14.10.2025 (የተሻሻለ: 15:24 14.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የመልማት መብቷን በየትኛውም አይነት ጫና አታቆምም - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
ግብጽ በቅኝ ግዛት ዘመን ውሎች አባዜ ተጠምዳ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብና የአባይ ወንዝ ዙሪያ የምታደርጋቸውን ጠብ አጫሪ ንግግሮች ሚኒስቴሩ በመግለጫው በጽኑ አውግዟል።
“የግብጽ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሀገራቸው በናይል ተፋሰስ ሀገራት በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ የውሃ ጉድጓድ መቆፈሪያ እና የዝናብ መሰበብሰቢያ መሠረተ ልማቶችን ጨምሮ አነስተኛ ይዞታ ያላቸውን ፕሮጀክቶችን በመገንባት ከአፍሪካ ጋር አጋርነቷን እያሳየች ነው ማለታቸው የግብጽን እውነተኛ ያልሆነና የተገደበ የቀጣናዊ ትብብር ፍላጎት ማሳያ አለመሆኑን” ሚኒስቴሩ ጠቅሷል።
በውሃ ሃብት ልማት በትብብር ለመሥራት የሁሉም የናይል ተፋሰስ ሀገራት የናይል ወንዝን በፍትሐዊነት የመጠቀም ይሁንታ እንደሚያስፈልግ በመግለጽ፤ የግብፅ ምናባዊ የትብብር ፕሮጀክት ግን እውቅና እንደሌለው አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ በመግለጫው ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዘላቂ አጠቃቀም ላይ ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጧል፡፡
ኢትዮጵያ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሌም ዝግጁ መሆኗንም ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X