አራት የኢትዮጰያ ባንኮች በአፍሪካ 100 ምርጥ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ ደረጃቸውን አሻሻሉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአራት የኢትዮጰያ ባንኮች በአፍሪካ 100 ምርጥ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ ደረጃቸውን አሻሻሉ
አራት የኢትዮጰያ ባንኮች በአፍሪካ 100 ምርጥ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ ደረጃቸውን አሻሻሉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.10.2025
ሰብስክራይብ

አራት የኢትዮጰያ ባንኮች በአፍሪካ 100 ምርጥ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ ደረጃቸውን አሻሻሉ

የአፍሪካ ቢዝነስ መጽሔት ባወጣው የ2025 የአፍሪካ 100 ምርጥ ባንኮች ደረጃ ዝርዝር ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 29ኛ ደረጃውን ሲያስጠበቅ አራት ተቋማት በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻል አሳይተዋል፡፡

አዋሽ ባንክ አ.ማ. 18 ደረጃዎችን በማሻሻል 50ኛ ደረጃን ይዟል፣

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከ44ኛ ወደ 43ኛ ከፍ ብሏል፣

ዳሽን ባንክ በ16 ደረጃዎች ከፍ ብሎ 71ኛ ሆኗል፣

አቢሲኒያ ባንክ በ17 ደረጃዎች ከፍ ብሎ 72ኛ ሆኗል፡፡

በ100 ምርጥ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ በ2014 ሁለት ባንኮች የነበሯት ኢትዮጵያ ዘንድሮ 93ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ዝርዝሩ የተካተተው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት ስድስት ባንኮችን ማካተት ችላለች፡፡

አህጉራዊ ደረጃን የሚመሩ ባንኮች፦

ስታንዳርድ ባንክ ግሩፕ (13.2 ቢሊዮን ዶላር) መሪነቱን አስቀጥሏል፣

የግብፅ ብሔራዊ ባንክ (7.3 ቢሊዮን ዶላር)

የሞሮኮው አቲጃሪዋፋ ባንክ (6.2 ቢሊዮን ዶላር)

◻ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ኬንያ በአስር ባንኮች መሪነቱን ይዛ ብትቀጥልም፤ የኢትዮጵያ ባንኮች በምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ዘርፍ ተወዳዳሪነታቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0