ሩሲያ እና ቻይና በዚህ ዓመት በሰሜናዊው የባሕር መስመር አዲስ የኮንቴይነር ማጓጓዝ ሪከርድ ለማስመዝገብ ተዘጋጅተዋል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ እና ቻይና በዚህ ዓመት በሰሜናዊው የባሕር መስመር አዲስ የኮንቴይነር ማጓጓዝ ሪከርድ ለማስመዝገብ ተዘጋጅተዋል
ሩሲያ እና ቻይና በዚህ ዓመት በሰሜናዊው የባሕር መስመር አዲስ የኮንቴይነር ማጓጓዝ ሪከርድ ለማስመዝገብ ተዘጋጅተዋል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.10.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና ቻይና በዚህ ዓመት በሰሜናዊው የባሕር መስመር አዲስ የኮንቴይነር ማጓጓዝ ሪከርድ ለማስመዝገብ ተዘጋጅተዋል

የኮንቴይነር ማጓጓዝ መጠኑ ከ400 ሺህ ቶን ሊበልጥ እንደሚችል የሮሳቶም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሌክሲ ሊካቼቭ ተናግረዋል፡፡

በዚህም የሩሲያ-ቻይና ትብብር በፍጥነት እያደገ መምጣቱ ማሳያ ነው ተብሏል። የኮንቴይነር ማጓጓዝ ሂደቱ በ2023/24 መጀመሪያ በእጥፍ በመጨመር፤ በአሁኑ ጊዜ በግምት በ60 በመቶ እያደገ ነው።

ሁለቱ ሀገራት ዘላቂ የትራንስፖርት ኮሪደር ለመፍጠር በሚል ዓላማ በሰሜናዊው የባሕር መስመር የባሕር ትራንስፖርትን ለማልማት የሚያስችል የድርጊት መርሃ ግብር አጽድቀዋል።

ዘመናዊ የሎጂስቲክስ እና የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች "የባሕር ትራንስፖርትን ውጤታማነት ለማሻሻል እና የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ለማልማት" ተግባራዊ ይሆናሉ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ከቻይና ወደ አውሮፓ በሰሜናዊው የባሕር መስመር በኩል የተላከው ኮንቴይነር ወደ ብሪታንያ የፊሊክስቶው ወደብ መደረሱ ሌላው ትልቅ ክንውን ተደርጎ ተወስዷል። በሩሲያ አርክቲክ በኩል ያለው ጉዞ 20 ቀናት የፈጀ ሲሆን ይህም በቀድሞ የደቡባዊ መስመሮች ከሚፈጀው ጊዜ ግማሽ ያህል ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0