የአፍሪካ ኅብረት ለማዳጋስካር ቀውስ አህጉራዊ የሽምግልና ጥረቶችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገለፀ
11:40 14.10.2025 (የተሻሻለ: 11:44 14.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ኅብረት ለማዳጋስካር ቀውስ አህጉራዊ የሽምግልና ጥረቶችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ኅብረት ለማዳጋስካር ቀውስ አህጉራዊ የሽምግልና ጥረቶችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገለፀ
መግለጫው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት፤ ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊና ከሀገር መውጣታቸው ከተዘገበ በኋላ በማዳጋስካር ያለውን ሁኔታ በተመለከተ አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጉን ተከትሎ የመጣ ነው።
◻ ከደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ እና ከህንድ ውቅያኖስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር "ሰላማዊ፣ ሁሉን አቀፍ እና አፍሪካ መር የመፍትሄ ሂደትን" ለመደገፍ ዝግጁ ነኝ ብሏል።
ኅብረቱ "ማንኛውንም ሕገ-መንግሥታዊ ያልሆነ የመንግሥት ለውጥ በጽኑ እንደማይቀበል" በድጋሚ ያስታወቀ ሲሆን፤ "በእርጋታ እና በሕገ-መንግሥታዊ ማዕቀፍ ውይይት ማድረግ" አስፈላጊ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X