ናይጄሪያ የተዘረፉ ቅርሶችን ለማስመለስ የምታደርገው ጥረት ጠንካራ ድጋፍ እንዲያገኝ ጠየቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱናይጄሪያ የተዘረፉ ቅርሶችን ለማስመለስ የምታደርገው ጥረት ጠንካራ ድጋፍ እንዲያገኝ ጠየቀች
ናይጄሪያ የተዘረፉ ቅርሶችን ለማስመለስ የምታደርገው ጥረት ጠንካራ ድጋፍ እንዲያገኝ ጠየቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.10.2025
ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ የተዘረፉ ቅርሶችን ለማስመለስ የምታደርገው ጥረት ጠንካራ ድጋፍ እንዲያገኝ ጠየቀች

የናይጄሪያ ኢዶ ግዛት መንግሥት ባሕል ቅርስን መልሶ በማግኘት ረገድ ያለውን ሚና አጉልቶ እንደሚያሳይ በመጥቀስ፤ የተዘረፉ የቤኒን የጥበብ ሥራዎችን ወደ ሀገር የመመለስ ጥረት ቀጣይ ድጋፍ እንዲያገኝ ጥሪ አቅርቧል ሲሉ የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በ1897ቱ የቤኒን ሥርወ መንግስት ላይ በብሪታንያ የተፈፀመውን ወረራ መነሻውን ያደረገው "ኦሳሜዴ" የተሰኘው ፊልም በቤኒን ከተማ ሲመረቅ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም እና የፈጠራ ኢኮኖሚ ዘርፍ የገዥው ከፍተኛ ልዩ ረዳት ዶ/ር ሙኒራት ለኪ፤ ፊልሙን "በተዝናኖት አማካኝነት የባሕል ጥበቃ ጉልህ ምሳሌ" ሲሉ ገልፀውታል።

“ታሪካችንን ለማካፈል ጠቃሚ ነው። ዛሬ ዓለም ስለ ቤኒን ታላቅ ግንብ (ሞአት) እና ስለ ነሐስ ቅርሶች መመለስ እያወራ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ፊልም አሁን መውጣቱ ወቅታዊ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ልዩ ረዳቱ በንግግራቸው ኦሳሜዴ ትክክለኛ ታሪክ አተራረክ እንዴት ቱሪዝምን እና ወጣቶችን ማሳተፍ እንደሚችል እንደሚያሳይ አፅንዖት ሰጥተዋል። የፊልሙ ፕሮዳክሽንም በኦሶሶ እና ፉጋር አካባቢዎች ሥራዎችን በመፍጠር እና የነጋዴዎችን ተሳትፎ በማሳደግ የአካባቢውን ኢኮኖሚ እንዳሳደገ አክለዋል።

የኦሳሜዴ ዋና አዘጋጅ ሊሊያን ኦሉቢ ፊልሙን ለቤኒን ሕዝብ "የካሳ ክፍያ" ሲሉ ጠርተውታል። ዋናዋ ተዋናይት ኢቪ ኦኩጃዬ ኤግቦህ ደግሞ በቤኒን ውስጥ መተወን ጥልቅ ትርጉም እንደነበረው ተናግራለች።

“በእውነተኛው ንጉሳዊ መንግሥት ስርዓት የቤኒን ተዋጊን ሚና በመጫወት፤ የቀድሞ አባቶቻቸውን እንደምናከብር አውቅ ነበር።”

ዳይሬክተር ጀምስ ኦሞክዌ የይዘቱን ትክክለኛነትን ለማረጋገጥ ቡድኑ ከቤኒን የታሪክ ምሁራን ጋር የፈጠረውን ትብብር አውስተዋል። ተዋናይ ዊሊያም ቤንሰን ደግሞ የተመልካቾችን ምላሽ "በእነሱ ላይ የተንፀባረቀ ኩራት" ሲል ገልጾታል።

ኦሳሜዴ ጥቅምት 7 በናይጄሪያ ሲኒማ ቤቶች መታየት የሚጀምር ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በእንግሊዝ ጥቅምት 21፣ 2018 እና በሰሜን አሜሪካ ጥቅምት 28 ለዕይታ እንደሚበቃ ተጠቁሟል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0