የደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የጎብኝዎች ፍሰት በነሀሴ ወር የ30 በመቶ እድገት አሳየ
10:13 14.10.2025 (የተሻሻለ: 10:14 14.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የጎብኝዎች ፍሰት በነሀሴ ወር የ30 በመቶ እድገት አሳየ
ከፍተኛ ቁጥር በተመዘገበበት የነሀሴ ወር፤ ደቡብ አፍሪካ 935 ሺህ 738 ዓለም አቀፍ ጎብኝዎችን ማስተናገዷ የቱሪዝም ዘርፉ ይበልጥ እንዲነቃቃ አድርጎታል ሲሉ ሚኒስትሩ ፓትሪሺያ ዴ ሊል በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
እ.ኤ.አ ከጥር እስከ ነሐሴ 2025 ሀገሪቱ 6.79 ሚሊዮን ቱሪስቶችን የተቀበለች ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ15.8 በመቶ እድገት የታየበት ነው፡፡
በሰነዱ መሠረት የደቡብ አፍሪካ የቱሪዝም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እድገት እያስመዘገበ ይገኛል። ለዚህ መሻሻል ዋነኞቹ ምክንያቶች፦
🟠 የቪዛ ማሻሻያ፣
🟠 ውጤታማ ግብይት፣
🟠 የዘርፉ የመቋቋም አቅም።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X