ግብፅ የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሊሻን ለዶናልድ ትራምፕ ልታበረክት ነው
18:26 13.10.2025 (የተሻሻለ: 18:34 13.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ግብፅ የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሊሻን ለዶናልድ ትራምፕ ልታበረክት ነው
ሽልማቱ ትራምፕ የጋዛ ጦርነት እንዲያበቃ ባደረጉት ወሳኝ ሚና እና ለሰላም ጥረቶችና ግጭት አፈታት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት የሚበረከትላቸው እንደሆነ የግብፅ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ትራምፕ በጥቅምት ወር መጀመሪያ እስራኤል እና የፍልስጤም ቡድን ሃማስ በጋዛ ሰርጥ ያለውን ግጭት ለመፍታት የሰላም ዕቅዱን የመጀመሪያ ምዕራፍ ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ እንደደረሱ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው።
በሌላ በኩል የእስራኤል ፕሬዝዳንት ኢሳቅ ሄርዞግ ለትራምፕ የሀገሪቱን ከፍተኛ የሲቪል ክብር፤ የፕሬዝዳንታዊ የክብር ሜዳሊያ፤ ለመሸለም መወሰናቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X