በሀገር በቀል የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች ማመን መጀመር አለብን - የዘርፉ ባለሙያ
17:39 13.10.2025 (የተሻሻለ: 17:44 13.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሀገር በቀል የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች ማመን መጀመር አለብን - የዘርፉ ባለሙያ
የአፍሪካ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ቁልፍ ተግዳሮት የክህሎት ክፍተት ሳይሆን፤ ዕድሎችን የማስፋት ውስንነት መሆኑን የኮንቬክስ ቴክኖሎጂስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኖርማን ኦንደጎ ይናገራሉ።
ኃላፊው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ አኅጉሪቱ ለተቀረው የዓለም ማሻገር የምትችላቸው በርካታ የፈጠራ ውጤቶች ባለቤት መሆኗን አንስተዋል።
"ለምሳሌ አንደ ኤም-ፔሳ እና ቴሌብር ያሉ ፈጠራዎችን ተመልከት። በትራንስፖርት ዘርፉም ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ራይድ ያሉ ከተቀረው የዓለም ክፍል ጋር የሚስተካከሉ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አሉ" ብለዋል።
ሁሉን አቀፍ ግዙፍ የኢንዱስትሪ ሁነት የሆነው ''እንቆጳ ጉባኤ'' ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X