ኢትዮጵያዊቷ ሃዊ ፈይሳ በታሪክ አምስተኛዋ ፈጣን ሴት አትሌት መሆን ቻለች
16:24 13.10.2025 (የተሻሻለ: 16:34 13.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያዊቷ ሃዊ ፈይሳ በታሪክ አምስተኛዋ ፈጣን ሴት አትሌት መሆን ቻለች
የ2025 የቺካጎ ማራቶን የሴቶች ውድድርን በአስደናቂ ብቃት 2:14:56 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ የምንግዜም አምስተኛዋ ፈጣን ሴት ሯጭ በመሆን አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ መቻሏን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡
ሃዊ ውድድሩን ተቆጣጥራ የመራችበት መንገድ፣ ከ30 ኪሎ ሜትር በኋላ በብቸኘነትና በበለጠ ፍጥነት መምራቷ ርቀቱን ከጨረሱ ሴቶች ሁሉ ፈጣኗ እንድትሆን አድርጓታል።
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት መገርቱ አለሙ በ2:17:18 በመግባት 2ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።
በወንዶች ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች አትሌት ሁሰዲን መሀመድ እና አትሌት ሰይፉ ቱራ 5ኛ እና 6ኛ ደረጃን በቅደም ተከተል ይዘዋል። ኡጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ በ2:02:23 ውድድሩን አሸንፏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X