ሩሲያ በምዕራብ ሰሃራ ያላት አቋም በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎች የሚመራ ነው - ላቭሮቭ
12:53 13.10.2025 (የተሻሻለ: 13:04 13.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ በምዕራብ ሰሃራ ያላት አቋም በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎች የሚመራ ነው - ላቭሮቭ
ለረጅም ጊዜ መሠረታዊ መርህ የነበረው ለምዕራብ ሰሃራ ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ሲሆን ይህም በሕዝበ ውሳኔ እንዲሆን የታሰበ ነበር ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
ሩሲያ የሞሮኮን የራስ ገዝ አስተዳደር እቅድ ሁሉም ተሳታፊ ወገኖች ከተስማሙበት ብቻ እንደሆነ የምትቀበለው አክለዋል።
አሜሪካ በፕሬዝዳንት ትራምፕ የመጀመሪያ የሥልጣን ዘመን ምዕራባዊ ሰሃራን የሞሮኮ አካል አድርጋ የአንድ ወገን እውቅና በመስጠት ጉዳዩ ተዘግቷል ብትልም፤ ሩሲያ ሁሉንም የሚያስማማ ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ አጥብቃ ታስገነዝባለች ሲሉ ላቭሮቭ ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎች አሁን ያሉት ብቸኛና ትክክለኛ ማዕቀፍ ናቸው ያሉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ሩሲያ አዳዲስ ውሳኔዎችን ለመቀበል ዝግጁ የምትሆነው ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቀረቡት የመግባቢያ መርሆዎች ላይ ከተስማሙ ብቻ ነው ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X