ሩሲያ የጋዛ ቀውስ ዳግም ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት አላት - ሰርጌ ላቭሮቭ
12:05 13.10.2025 (የተሻሻለ: 12:14 13.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ የጋዛ ቀውስ ዳግም ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት አላት - ሰርጌ ላቭሮቭ
ሞስኮ በሻርም ኤል-ሼክ የሚካሄደው የጋዛ የሰላም ጉባኤ ስኬታማ እንዲሆን ከልብ ትመኛለች ሲሉ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከዓረብ ሀገራት ለተወጣጡ የመገናኛ ብዙኃን መግለጫ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡
ሰርጌ ላቭሮቭ ያነሷቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦
◻ ሩሲያ ሁሉም የሚመለከታቸው ሀገራት የጋዛ ቀውስ ዳግም እንዳይከሰት እንዲከላከሉ ጥሪ ታቀርባለች፡፡
◻ የትራምፕ የጋዛ እቅድ በጠረጴዛው ላይ ያለ የተሻለው እቅድ ቢሆንም የፍልስጤምን ችግር አይፈታም።
◻ የፍልስጤም ግዛት ሳይፈጠር የመካከለኛውን ምስራቅ ግጭት በዘላቂነት መፍታት አይቻልም፡፡
◻ በጋዛ ዙሪያ በተደረጉ ለውጦች ምክንያት የሩሲያ-አረብ ስብሰባ ተላልፏል፤ በአዲስ ቀን ዙሪያ ስምምነት ሲደረስ ይከናወናል፡፡
◻ የትራምፕ የሰላም እቅድ የጋዛን ብቻ ሳይሆን የዌስት ባንክን እጣ ፈንታ መግለጽ አለበት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X