ዩክሬን ከዳኢሽ* የሽብር ቡድን ጋር በመተባበር በሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ባለሥልጣን ላይ ልትሰነዝር የነበረው የሽብር ጥቃት ከሸፈ
10:41 13.10.2025 (የተሻሻለ: 10:44 13.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዩክሬን ከዳኢሽ* የሽብር ቡድን ጋር በመተባበር በሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ባለሥልጣን ላይ ልትሰነዝር የነበረው የሽብር ጥቃት ከሸፈ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዩክሬን ከዳኢሽ* የሽብር ቡድን ጋር በመተባበር በሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ባለሥልጣን ላይ ልትሰነዝር የነበረው የሽብር ጥቃት ከሸፈ
የሩሲያ ደህንነት አገልግሎት እንደገለጸው፤ በሩሲያ እና በኡዝቤኪስታን ባለሥልጣናት በዓለም አቀፍ ደረጃ በቁጥጥር ስር እንዲውል ሲፈለግ የነበረውና በዳኢሽ* አስተባባሪነት የሚመራው ቀጥተኛ ፈጻሚውን ጨምሮ አራት ሰዎች ታስረዋል።
የዳኢሽ ወኪል በዩክሬን ወታደራዊ የስለላ ድርጅት በተፈጸመው የጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ግድያ ውስጥ እጁ እንዳለበት የፌደራል ደህንነት አገልግሎት ጠቁሟል።
ኪሪሎቭ እና ረዳታቸው በታህሳስ 2024 በሞስኮ በሚገኘው የመኖሪያ ሕንፃቸው መግቢያ አጠገብ ቆሞ የነበረ ስኩተር ውስጥ የተደበቀ ፈንጂ በመፈንዳቱ ህይወታቸው አልፏል።
*ዳኢሽ (አይኤስአይኤስ/አይኤስአይኤል/አይኤስ በመባልም ይታወቃል) በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ግዛቶች የታገደ የሽብር ድርጅት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X