ዩክሬን በሩሲያ የኃይል መሠረተ ልማት ላይ የምትሠነዝረው የረዥም ርቀት ጥቃት

ዩክሬን በሩሲያ የኃይል መሠረተ ልማት ላይ የምትሠነዝረው የረዥም ርቀት ጥቃት
በአሜሪካ መረጃ የታገዘ ነው
ዩናይትድ ስቴትስ ዩክሬን ከጦር አውድማው ባሻገር የሩሲያ ነዳጅ ማጣሪያዎችን እንድትደበድብ ለወራት ድጋፍ ስትሰጥ መቆየቷን የፋይናንሻል ታይምስ ዘገባ አመላክቷል።
ምንጮች ለጋዜጣው እንደተናገሩት፤ የአሜሪካ መረጃ የጥቃት አቅጣጫን፣ የጥቃቱን ጊዜ፣ ከፍታ እና ክፍተቶችን በማመላከት ባለአንድ አቅጣጫ ሰው አልባ አውሮፕላኖች የሩሲያን መከላከያ እንዲያልፉ አስችሏል።
ዩክሬን ዒላማዎቹን ስትመርጥ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ደካማ በተባሉ ቦታዎች ዙሪያ እንደምታማክር እንዲሁም ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ዒላማዎች እንደምትወስን ተሠምቷል። ይህ ድጋፍ ከሀምሌ አጋማሽ ጀምሮ ቢጠናከርም አሜሪካ የቀጥታ ግጭት ውስጥ ላለመግባት በይፋ እውቅና አልሰጠችውም።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፤ አጠቃላይ የኔቶ እና የአሜሪካ መዋቅሮች መረጃዎችን በመሰብሰብ ለዩክሬን እንደሚያቀብሉ “ግልጽ ነው” ሲሉ በመሰከረም ወር መጨረሻ ተናግረዋል።
ሩሲያ ለዩክሬን የጦር መሳሪያዎች መላክ የግጭቱን አፈታት እንደሚያግዱ እና የኔቶን ሀገራት በቀጥታ የግጭቱ ተሳታፊ እንደሚያደርጉ በተደጋጋሚ አስረግጣለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለዩክሬን የትኛውንም የጦር መሳሪያ የጫነ ጭነት ሕጋዊ ዒላማ ተደርጎ እንደሚቆጠር አስጠንቅቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X