የማዳጋስካር ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንቱ በ48 ሰዓታት ውስጥ እንዲነሱ አስጠነቀቁ
18:28 12.10.2025 (የተሻሻለ: 18:34 12.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የማዳጋስካር ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንቱ በ48 ሰዓታት ውስጥ እንዲነሱ አስጠነቀቁ
ተቃዋሚዎቹ ሕግ አውጪዎች አንድሪ ራጆሊና ከሥልጣን እንዲወገዱ በ48 ሰዓታት ውስጥ ድምፅ ካልሰጡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ እንዲፈርስ ግፊት እንደሚያደርጉ ዝተዋል።
ማስጠንቀቂያ ያስተላለፉት ባባ በመባል የሚታወቁት የተቃዋሚ ፓርቲ አባል እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት ምክር ቤት አባል አልባን ራኮቶአሪሶአ ናቸው።
የማዳጋስካር "ጄን ዚ" ትውልድ ንቅናቄውን አጠናክሯል፦
▪ተቃዋሚዎች ግፊቱን ለመጨመር ከሰኞ ጀምሮ ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ጥሪ እያቀረቡ ነው። ዋና ዓላማቸው ፕሬዝዳንቱ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ማስገደድና ዋና ዋና ማሻሻያዎችን ማስፈጸም ነው።
▪ ተቃዋሚዎች ግንቦት 13 አደባባይ የሚደረገውን ንቅናቄ እንዲቀላቀሉ ለማሳሰብ ሁሉንም የመንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ለመጎብኘት አቅደዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X