የ31 ብሔር ብሔረሰቦች ባሕላዊ ምግቦች የቀረቡበት የምግብ ፌስቲቫል ተካሄደ
18:17 12.10.2025 (የተሻሻለ: 18:24 12.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የ31 ብሔር ብሔረሰቦች ባሕላዊ ምግቦች የቀረቡበት የምግብ ፌስቲቫል ተካሄደ
የቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት ከኩሪፍቱ አፍሪካ ቪሌጅ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ፌስቲቫል፤ ባሕላዊ ምግቦችን የማስተዋወቅ፣ ወደ ገበታ እንዲመጡ ማድረግ እንዲሁም የምግብ ቱሪዝምን የማሳደግ ዓላማ ያነገበ ነው።
በሌላ በኩል በእውቀት ሽግግር እና ሥራ ፈጠራ በኩል አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል።
የቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ የሚገኙ ባሕላዊ የምግብ ዓይነቶች በሆቴሎች የምግብ ሜኑ ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ መግለፁ የሚታወስ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ