ሩሲያ ለዓለም አቀፍ ገበያ የምግብ ምርት ከሚያቀርቡት ውስጥ ዋነኛዋ ነች - ፑቲን
17:58 12.10.2025 (የተሻሻለ: 18:04 12.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ ለዓለም አቀፍ ገበያ የምግብ ምርት ከሚያቀርቡት ውስጥ ዋነኛዋ ነች - ፑቲን
የሩሲያ ፕሬዝዳንት የሩሲያ የግብርና ሠራተኞችን ቀን በማስመልከት በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሀገሪቱ የግብርና ዘርፉን ዕድገት መደገፏን፣ ተወዳዳሪነቱን እና የቴክኖሎጂ ነጻነቱን ማሳደጓን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
"የእኛ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ምርቶች፤ እህል፣ የአትክልት ዘይቶች፣ ዓሣ፣ ጣፋጭ ምግቦች እና ሌሎች ሸቀጦች በዓለም ዙሪያ ከ160 በላይ ሀገራት ዘንድ ይታወቃሉ፤ ተፈላጊዎችም ናቸው" ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል።
የሩሲያ የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኤክስፖርት ልማት ማዕከል ባወጣው መረጃ መሠረት፤ ከጥር እስከ ነሐሴ 2017 ዓ.ም ሩሲያ ከ2.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን 11 ሚሊዮን ቶን የሚጠጉ የግብርና ምርቶች ለአፍሪካ ሀገራት ልካለች።
እህል እና የጥራጥሬ ሰብሎች የሩሲያ ዋነኛ የውጭ ንግድ ምርቶች ሲሆኑ ባለፈው ዓመት ብቻ ከ75 ሚሊዮን ቶን በላይ ምርት ለውጭ ገበያ ተልኳል። ሩሲያ በስንዴ፣ ገብስ እና በክዊት ከዓለም ቀዳሚ፤ በአተር እና በሽምብራ ምርት ደግሞ ከዓለም ሁለተኛ ትልቋ ላኪ ሀገር ናት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X