በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፋብሪካ ለመገንባት ከአውሮፓ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተደረሠ
17:00 12.10.2025 (የተሻሻለ: 17:04 12.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፋብሪካ ለመገንባት ከአውሮፓ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተደረሠ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፋብሪካ ለመገንባት ከአውሮፓ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተደረሠ
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በረኦ ሐሰን መሠረቱን አውሮፓ ካደረገው ባትስዋፕ አውቶሞቲቭ ኃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል።
ትብብሩ አዲስ አበባ ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ማምረቻ ፋብሪካ መትከል፣ የባትሪ ማምረቻ እና ጥናትና ምርምር እንዲሁም የአረንጓዴ ትራንስፖርት ዘርፍ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማቋቋምን ያካትታል።
በ2026 በሚጀምረው የስምምነቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ 240 የሙከራ የኤሌክትሪክ ጭነት ተሽከርካሪዎች ሲገነቡ፤ 10 አውቶማቲክ የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎች በአዲስ አበባ ይዘረጋሉ።
ስምምነቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአረንጓዴ እንቅስቃሴ ዘርፍ ቁልፍ ተዋናይ ከመሆን ራዕይዋ ጋር የተጣጣመ ነው ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X