በሲሼልስ ምርጫ በሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት በተቃዋሚ መሪው ተሸነፉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሲሼልስ ምርጫ በሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት በተቃዋሚ መሪው ተሸነፉ
በሲሼልስ ምርጫ በሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት በተቃዋሚ መሪው ተሸነፉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.10.2025
ሰብስክራይብ

በሲሼልስ ምርጫ በሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት በተቃዋሚ መሪው ተሸነፉ

የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን የቀድሞ የፓርላማ አፈ-ጉባኤ እና የሕክምና ዶክተር ፓትሪክ ሄርሚኒ ከማጣሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው 52.7 መቶ ድምፅ በማግኘት ፕሬዝዳንት ዋቨል ራምካላዋን ድል እንዳደረጉ አስታውቋል።

ሄርሚኒ በድል ንግግራቸው “ይህንን ሥልጣን በአመስጋኝነት፣ በታላቅ የኃላፊነት ስሜት እና በሲሼልስ ሕዝብ ጥንካሬና ፅናት የማያወላውል እምነት እቀበላለሁ” ብለዋል።

የሄርሚኒ ፓርቲ ዩናይትድ ሲሼልስ፤ ራምካላዋን እ.ኤ.አ በ2020 ከማሸነፋቸው በፊት ከ40 ዓመታት በላይ ሀገሪቱን የመራ ሲሆን አሁን በፓርላማ አብላጫ መቀመጫ መልሶ በማግኘት ወደ ሥልጣን ተመልሷል።

ዩናይትድ ሰይሼልስ በምርጫ ማኒፌስቶው ላይ የሚከተሉትን አቅዷል፦

🟠 የማህበራዊ ድጋፍ እርምጃዎችን እንደገና ማስጀመር፣

🟠 ሥራ አጥነትን መቀነስ እና

🟠 የጡረታ ማህበራዊ ዋስትና ጥቅማጥቅሞችን መጨመር ናቸው።

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሄርሚኒ ድል የእንኳን ደስ አለሆት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0